መሪውን በምርጫ የሚሾም እና የሚሽር ማኅበረሰብ ለመገንባት ምሁራን የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል።

3

 

ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምርጫ ዜጎች መብታቸውን የሚያረጋግጡበት ነው።

በዴምክራሲያዊ የምርጫ ሂደት ቅቡልነት ያለው መንግሥት እየተመረጠ ወደ ሥልጣን እንዲመጣ ይደረጋል። በዚህ ሂደት ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ይኾን ዘንድ ደግሞ ምሁራን ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ይታመናል።

በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የፓለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህር እንቢአለ በየነ (ዶ.ር) እንደሚሉት ምሁራን ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉልህ ድርሻ አላቸው። በተለይም በምርጫ ወቅት ዜጎች በዕውቀት እና በዕውነት ላይ የተመሠረተ ግንዛቤ ኖሯቸው በንቃት እንዲሳተፉ የማድረግ ኀላፊነት አለባቸው።

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ምሁራን የድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ከምሁራን የሚጠበቁ ጉዳዮችን ሲያብራሩ እንዳሉትም፦

📌ማኅበረሰቡን ማስተማር እና ግንዛቤ መፍጠር፤

🗡በምርጫ ወቅት ሙያዊ ዕውቀትን በመጠቀም ሳይንሳዊ በመኾነ መንገድ ምርጫው እንዲካሄድ አስቻይ ነገሮችን መፍጠር ይጠበቅባቸዋል።

📌ከምርጫ ጋር የተያያዙ ምርምሮችን በማድረግ በተለይም ጠንካራ የምርጫ ሥርዓት እንዲገነባ ማድረግ ያስፈልጋል።

📌ዓለም አቀፋዊ የምርጫ ሂደቶችን እና ተሞክሮዎችን ቀስሞ እና ቀምሮ ማምጣት፤ የዓለም ሀገራት ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንዴት እንዳከናወኑ ተሞክሮውን ለሕዝቡ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መሥራት እንደሚገባቸው ነው የገለጹት።

📌ምርጫ የሀገርን ዕጣ ፈንታ የሚወሰን መሠረታዊ ጉዳይ በመኾኑ ለቀጣዩ ትውልድ የዳበረ የዴሞክራሲ ባሕልን ለማስረከብ ጠንካራ ተቋማዊ አሠራር ማዳበር ይገባልም ነው ያሉት።

በምርጫ ባለመሳተፍ ለውጥ አይመጣም ያሉት ምሁሩ በምርጫ በመሳተፍ ሰላማዊ እንዲኾን ከማድረግ ባለፈ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል።

ምሁራን ለየትኛውም ወገን ሳይወግኑ፣ ጥልቅ ዕውቀታቸውን በመጠቀም ለሕዝብ እና ለሀገር የሚበጀውን ምልከታ በግልጽ መተንተን እና ማስረጽ ይኖርባቸዋል።

ምሁራን በመራጭነት በመሳተፍ፣ ሕግ እና ሥርዓትን ተከትለው ለሌላው ማኅበረሰብ ግንባር ቀደም አርዓያ መኾን ይጠበቅባቸዋል።

በተለይም ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ወቅት እና ከምርጫ በኃላ በንቃት በምሁራዊ ዕይታ መሳተፍ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

ከባለፉት ዓመታት የተሻለ የምርጫ ሥርዓት እንዲከወን ሁሉም ባለቤት መኾን ይጠበቃል ብለዋል።

መሪውን በምርጫ የሚሾም እና የሚሽር ሕዝብ በመገንባት ሂደት ላይ እንደ ሀገር ምሁራን የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አመላክተዋል።

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

#የ7ኛው_ ጠቅላላ_ምርጫ_አማራ_ክልል #Ethiopia 🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“የምርጫውን ደኅንነት መጠበቅ የሚሊሻ ኃይሉ ቀዳሚ ጉዳይ ነው” ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ
Next articleብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው።