ምርጫው ሠላማዊ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ የሠላም ዘብ መሆን እንዳለበት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

2

 

ጎንደር :ሚያዝያ 30/2018ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያውን የምርጫ ቅስቀሳ እና የድጋፍ ሠልፍ አካሂዷል።

በምርጫ እጬ ትውውቅ እና ምርጫ ቅስቀሳ ሁነቱ ላይ የተገኙት የከተማዋ ኗሪዎች ምርጫው ለሠላም እና ለሀገር ግንባታ የተሻለ እንዲሆን ፓርቲውን ደግፈው መገኜታቸውን ገልፀዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች ምርጫው ሠላማዊ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ የሠላም ዘብ መሆን እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የማራኪ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ባህሩ ድረስ ምርጫው የተሳካ እንዲሆን እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ፓርቲው ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አስረድተዋል።

በተለይ በምርጫ ካርድ ምዝገባ ወቅት ጀምሮ ያለው እንቅስቃሴ እና እስከ ምርጫው ፍፃሜ ድረስ የክፍለ ከተማው የምርጫ ጣቢያዎች ሠላማቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲያከናውኑ ሥራዎች መሰራታቸውን አስረድተዋል።

የፓርቲው የክልል ምክር ቤት እጩ የሆኑት ባንቺ ይርጋ በጎንደር ከተማ አስተዳደር በክፍለ ክተማ ደረጃ የተደረገው የድጋፍ ሠልፍ የፓርቲውን ሪዮት ዓለም እና እየተገበራቸው ያሉ የልማት ሥራዎችን የተረዱ በርካታ ዜጎች መኖራቸው የተረጋገጠበት መሆኑን አስረድተዋል።

ምርጫው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅም ህብረተሰቡ በባለቤትነት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ተስፋየ ጋሹ

Previous article“በላይ አርማጭሆ ወረዳ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ውጤታማና ለሌሎች አካባቢዎች ተምሳሌት የሚኾን ነው” ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሜ በዶ
Next article“የምርጫውን ደኅንነት መጠበቅ የሚሊሻ ኃይሉ ቀዳሚ ጉዳይ ነው” ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ