“በላይ አርማጭሆ ወረዳ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ውጤታማና ለሌሎች አካባቢዎች ተምሳሌት የሚኾን ነው” ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሜ በዶ

2

 

ጎንደር: ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም ጎንደር የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሜ በዶ ፣ የአማራ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ብርቱካን ሲሳይ ፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አወቀ አስፌና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ የልማት ሥራዎችንና የምርጫ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሜ በዶ
የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ውጤታማና ለሌሎች አካባቢዎች ተምሳሌት የሚኾን እንደኾነ ገልጸዋል ።
በወረዳው የአትክልትና ፍራፍሬ ልማቶችን ፣ በእንስሳት ሃብት ልማት የነዎሪዎች ተጠቃሚነት ፣ በማኅበረሰቡና በመንግሥት የትምህርት ቤቶች ግንባታ እንዲሁም የዜጎችን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመሥጠት መዘጋጀታቸውን ጎብኝተዋል።

ምክትል አፈ ጉባኤዋ ዜጎች ያስተዳድረናል የሚሉትን ፖርቲ እንዲመርጡና ምርጫውም ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ ኾኖ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም አሳስበዋል ።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አወቀ አስፈሪ በበኩላቸው በላይ አርማጭሆ ወረዳ እየተከናወነ ያለው የልማት ሥራዎች በየጊዜው ልውጥ የሚታይበት ነው ብለዋል።

የወረዳው ነዋሪዎች በአትክልትና ፍራፍሬ እና በእንስሳት ሃብት ልማት ገቢያቸው እያደገ መምጣቱን ዋና አሥተዳዳሪው ጠቅሰዋል።

በእንስሳት ሃብት ልማት የተሰማሩት አቶ ተስፋማሪያም መለስና ወይዘሮ አደይነሽ መንግሥቱ በሥራው ውጤታማና ገቢያቸው እያደገ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

አቶ ተስፋማሪያም ከአንዲት ላም በቀን ከ28 እስከ 30 ሊትር ወተት እንደሚያገኙ ጠቅሰው ፤ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የመክፈት ህልም እንዳላቸው ተናግረዋል።

አቶ ተስፋማሪያም ለአሥር ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውንም ጠቅሰዋል።

ዘጋቢ:- ህይወት ኃይሉ

Previous articleየሚሊሻ ኀይሉ ሰላምን በማረጋገጥ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ እየሠራ ነው።
Next articleምርጫው ሠላማዊ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ የሠላም ዘብ መሆን እንዳለበት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።