ለአፍሪካ ጨለማን ሳይኾን እውነቷን እንግለጥ!

2

 

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓድዋ ሙዚየም እየተካሔደ ነው።

ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ሲኾን 400 ሚሊዮን ተከታይ እንዳለቸው ተገልጿል።

የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሥራ አሥኪያጅ ሰይፈ ደርቤ ይህ ስብስብ የአፍሪካን ገጽ በዲጂታል ዓለም የመግለጥ አቅምን የሚገነባ ነው ብለዋል።

ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የአፍሪካን አቅም ፈጠራ እና ክህሎት የምናሳድግበት ነው ሲልም ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አፍሪካ ጨለማ ሳይኾን የተሻለ አቅም እና ገጽታ ያለባት በመኾኗ እና ይህንን ለማሳየት ፐልስ ኦፍ አፍሪካን አቋቁመዋል። የአፍሪካን ትርታም ይገልጣል ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ይህ ስብስብ የአፍሪካን ጨለማ ሳይኾን እውነት እና መልካም ገጽታ የሚገለጥባት መኾኗን ማሳየት አለበት ነው ያሉት።

የጉባዔው አሥተባባሪ ገመዳ ኦላና ኢትዮጵያ አንዲሁ ሀገር አይደለችም ታሪክን፣ ባሕልን፣ እውነትን እና የተፈጥሮ ሀብቶችን ያቀፈች ሀብቷን ደግሞ አሁን በአግባቡ እየገለጠች ያለች ሀገር ነች ብለዋል።

ይህ ዕለትም የአፍሪካን የዲጂታል ንቅናቄ ውልደት እንደኾነ ነው የገለጹት። ተባብረን ለብሩህ አፍሪካ አንሥራ ብለዋል።

ዘጋቢ፦ አንዷለም መናን

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ከሚያዚያ 27/2018ዓ.ም ጀምሮ በተቋሙ ገጽ የሚለቀቁ መረጃዎች የኔ አይደሉም” የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Next articleየሚሊሻ ኀይሉ ሰላምን በማረጋገጥ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ እየሠራ ነው።