
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፌስቡክ ገጽ ከሚያዚያ 27/2018ዓ.ም ጀምሮ ከተቋሙ ቁጥጥር ውጭ መኾኑን ገልጿል።
የፌስቡክ ገጹ አድሚን የነበሩት እና የተቋሙ ዲን አስጨንቅ ካሳ በታጠቁ አካላት ታፍነው በመወሰዳቸው ገጹ ከተቋሙ ቁጥጥር ውጭ ኾኗል።
ገጹ ሀሰተኛ መረጃ እየተላለፉበት መኾኑንም ተቋሙ አሳውቋል።
በመኾኑም ከሚያዚያ 27/2018ዓ.ም ጀምሮ በተቋሙ ገፅጽ የሚለቀቁ መረጃዎች የተቋሙ አለመኾናቸውን አወቁልኝ ብሏል ኮሌጁ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
