የመገናኛ ብዙኃን ከጥላቻ ንግግርና ከሐሰተኛ መረጃ በመራቅ ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል!

3

 

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እና ድርጅቶች ከጥላቻ ንግግር እና ከሐሰተኛ መረጃዎች የጸዱ ዘገባዎችን በማቅረብ ለሀገር ሰላም ግንባታ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀርቧል።

ጥሪው የቀረበው “መጪውን ጊዜ ለሰላም መቅረፅ በዲጂታል ዓለም የፕሬስ ነፃነትን መጠበቅ” በሚል መሪ መልዕክት የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነው።

እንደ ኢቢሲ መረጃ የፕሬስ ነፃነት ሕገ-መንግሥታዊ መብት ብቻ ሳይኾን የመተማመንና የውይይት መሠረት መኾኑ ተነስቷል። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ብዝኃነት በሚታይባቸው ሀገራት የሚዲያ ሚና የልዩነት ድልድይ መኾን እንዳለበት በመድረኩ ተነስቷል።

በዲጂታል ዓለም የሚታየውን የተዛባ መረጃ ክፍተት በትክክለኛ መረጃ በመተካት እና ለማኅበረሰቡ በማድረስ ረገድ ጋዜጠኞች ያላቸውን የማይተካ ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠይቋል፡፡

መገናኛ ብዙኃን ግጭቶችን በማያባብስ መልኩ እና ሰዎች ተቀራርበው በሃሳብ እንዲወያዩ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መሥራት እንደሚገባቸውም በመድረኩ ተመላክቷል።

ጋዜጠኝነት በሥነ-ምግባር የታነጸ እና ሙያዊ ዲሲፕሊንን ያከበረ እንዲኾን እንዲኹም ጋዜጠኞች ለሰላም ዘብ የሚቆሙበት ምቹ ኹኔታ እንዲፈጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleምርጫው ሀገርን ያስቀደመ እንዲኾን እንሠራለን።
Next article“ከሚያዚያ 27/2018ዓ.ም ጀምሮ በተቋሙ ገጽ የሚለቀቁ መረጃዎች የኔ አይደሉም” የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ