ኢትዮጵያን በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ ለማድረግ እየተሠራ ነው።

1
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ብልጽግና ፓርቲ በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማው ፣ በክልሉ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ብልጽግና ፓርቲ ያከናወናቸው የልማት ሥራዎች አበረታች መኾናቸውን ገልጸዋል።
የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ ለማድረግ እየሠራ መኾኑን አንስተዋል።
በግብርና ፣ በኢንዱስትሪ ፣ በትምህርት ፣ በጤና​ እና በቱሪዝም ዘርፎች የታዩ ውጤቶች ሁሉን አቀፍ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።
በሁሉም የልማት ዘርፎች ሞዴል ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲመዘገብ እየተጋ መኾኑን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article