“ምርጫ ለሰላምና ዴሞክራሲ መሠረት ነው” የደብረ ብርሃን ነዋሪዎች

14
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ሥር በሚገኙ 5 ክፍለ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች፣ በመጪው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በንቃት እንደሚሳተፉ በአደባባይ ሰልፍ ገለልጸዋል።
​ነዋሪዎቹ በሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ምርጫ የሥልጡንነት መገለጫ ከመሆኑም ባለፈ ለዴሞክራሲ ግንባታና ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ መሠረት መኾኑን አንስተዋል።
ሂደቱ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ​ፍትሐዊ፣ ​ሚዛናዊ እና ነጻ ሆኖ እንዲከናወን አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
ሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ለሀገራዊ የምርጫ ሂደት ያላቸውን ከፍተኛ ተነሳሽነት ያሳየ እንደነበር ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

See less
Previous articleነጻ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ እንሠራለን።
Next article