ሀገራትን እየፈተነ ያለው ሰርጎ ገብ ጥቃት፦

10
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰርጎ ገብ ጥቃት ማለት አንድ ያልተፈቀደለት አካል (Hacker) ወደ ግለሰቦች ወይም ተቋማት የኮምፒውተር መረብ፣ ሲስተም ወይም ዳታቤዝ ሰብሮ በመግባት መረጃዎችን ለመሰረቅ፣ ለማጥፋት ወይም ሲስተሙን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ሙከራ ነው።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰርጎ ገብ ጥቃቶች በከፍተኛ ኹኔታ እየጨመሩ ነው። ለአብነት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኢትዮጵያ ላይ ከተሰነዘሩ ከ50 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መካከል “ሰርጎ ገብ (Intrusion)” ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል።
በኢመደአ መረጃ መሠረትም በ2018ዓ.ም በኢትዮጵያ ከተሞከሩ 50,155 የጥቃት ሙከራዎች ውስጥ የሰርጎ ገብ ጥቃቶች ብዛት፡ 20,601 ወይም 41በመቶ ነው።
👉ሰርጎ ገቦች የሚጠቀሟቸው ስልቶች፦
#የደህንነት ክፍተቶችን መፈለግ (Exploiting Vulnerabilities): በሲስተሞች ወይም ሶፍትዌሮች ላይ ያሉ ክፍተቶችን (Bugs) በመጠቀም መግባት
#ማጭበርበር (Phishing): በኢ-ሜይል ወይም በቴክስት መልዕክት አሳሳች ሊንኮችን በመላክ የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል በመስረቅ
#ደካማ የይለፍ ቃላት (Weak Passwords): በቀላሉ ሊገመቱ የሚችሉ የይለፍ ቃላትን በመሰበር መግባት
4. ተንኮል አዘል ሶፍትዌሮች (Malware): ቫይረሶችን ወደ ሲስተሙ በመርጨት የኋለኛ በር (Backdoor) በመክፈት።
🚫እንዴት መከላከል ይቻላል?
💪ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም፦ ፊደላት፣ ቁጥሮች እና ምልክቶችን ያካተተ ምስጢራዊ ቃል መጠቀም።
#ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (2FA)፦ ለፌስቡክ፣ ለኢሜይል እና ለሌሎች መተግበሪያዎች “Two-Factor Authentication” መተግበር።
#ሶፍትዌሮችን ማዘመን (Update)፦ ስልክ ወይም ኮምፒውተርን “Update” ሲጠይቅ ወዲያውኑ ማድረግ፤ ይህም አዳዲስ የደህንነት ክፍተቶችን ይደፍናል።
#የማይታወቁ ሊንኮችን አለመጫን፦ በኢሜይል ወይም በውስጥ መስመር የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን ከመክፈት መቆጠብ እና
#የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ማሳደግ እንደሚገባ የኢመደአ መረጃ ያሳያል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

See less
Previous articleምርጫን ለማደናቀፍ መሞከር ከፍተኛ የሕግ ተጠያቂነትን ያስከትላል።