
አዲስ አበባ፡ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎብኝተዋል።
በተለያዩ ዘርፎች አምራች ኢንዱስትሪዎች ይዘዋቸው የቀረቡትን ምርቶች የጎበኙት የሃይማኖት አባቶቹ በኤክስፖው የተመለከቱት ነገር እንደሀገር ኩራት እንዲሰማቸው ያደረገ መኾኑንም ገልጸዋል።
በሀገር ውስጥ ተኪ ምርትን በማምረት እና የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት ትልቅ ፍይዳ ያላቸው ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶች ወደገበያው መቀላቀል እንደ ሀገር የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ዕድገት አመላካች መኾኑንም ተናግረዋል።
የሀገር ውስጥ ምርቶች መበራከት አቅርቦት እና ፍላጎቱ እንዲመጣጠን በማድረግ በአነስተኛ ዋጋ ምርትን ለሸማቹ ማኅበረሰብ ማድረስ የሚያስችል መኾኑንም ገልጸዋል።
ግለሰቦች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት ለሀገር ውስጥ ምርት ትልቅ ቦታ በመስጠት መግዛት እንዳለባቸው እና አልፎ አልፎ የሚታዩ የግንዛቤ ክፍተቶችን መሙላት እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት 2018 ኤክስፖ ከ20 በላይ አምራቾች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፦ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
