በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የሚያለሙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግሮች ለመፍታት እየተሠራ ነው።

2
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል። ምልከታ ካደረጉባቸው ፋብሪካዎች ውስጥ በናይክ ትሬዲንግ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስር የሚገኘው አሚን የምግብ ዘይት ፋብሪካ ይገኝበታል።
የናይክ ትሬዲንግ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አሥኪያጅ አታላይ ወንዴ እንዳሉት ፋብሪካው በቀን እስከ 30 ሺህ ሊትር ዘይት የማምረት አቅም አለው።1 ሺህ ኩንታል ፋጉሎም ያመርታል። ለ127 ዜጎች የሥራ ዕድልም እንደሚፈጥርም ገልጸዋል። ድርጅቱ ምርቶቹን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ይሠራል ነው ያሉት።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ፋብሪካው ወደ ምርት መሸጋገሩ በገበያ ላይ ያለውን የዘይት እጥረት ለመቅረፍ እና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። ከአካባቢው አርሶ አደሮች የቅባት እህሎችን በመረከብ ያለምንም የጥሬ እቃ እጥረት ሥራውን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ባለሀብቶችም በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ የሥራ ዘርፋቸውን በማስፋት እንዲሠሩም ጠይቀዋል።
ከኀይል አቅርቦት፣ ከፋይናንስ እና ከቦታ ማስፋፊያ ጋር በተያያዘ የሚያግጥሙ ችግሮች የዘርፉ ፈተና እንዳይኾኑ ከተማ አሥተዳደሩ በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleየሀገር ውስጥ ምርት መበራከት አቅርቦት እና ፍላጎት እንዲመጣጠን ያደርጋል።