
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 85ኛው የአርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
ዕለቱን አስመልክተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ “ዛሬ የምናከብረው አባቶቻችን እና እናቶቻችን በፋሺስት ጣሊያን መርዛማ ጋዝ እየተለበለቡ ሕይወታቸውን ሰውተው ያጎናጸፉንን ታላቅ ድል ነው ብለዋል።
ድሉ ከተቀረው ዓለም እገዛን ባላገኘንበት ወቅት ሉዓላዊነታችን በራሳችን ያስጠበቅንበት እና ፋሺዝምን በአካልም ኾነ በአስተሳሰብ ማንበርከክ እንደሚቻል ለዓለም ያሳየንበት ቀን እንደኾነም ገልጸዋል።
በብርቱ ፈተናዎች መካከል የኢትዮጵያን ቀጣይነት ለማረጋገጥ መሠረታችን አባቶቻችን የከፈሉት መሥዋዕትነት ነው ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
“ጀግንነት ማለት ከሁሉም በላይ ሀገርን ማስቀደም ነው” ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ በከባድ ፈተናዎች ጸንታ የቆመች ብርቱ ሀገር መኾኗን መረዳት እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።
ባልተገራ የሥልጣን ፍላጎት እና ባልተገባ ድርጊት ላይ የተሠማሩ አካላት ኢትዮጵያን ማንበርከክ እንደማይችሉ ከታሪክ ሊማሩ ይገባል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ኢብራሒም መሐመድ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
