የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ገበያን በማረጋጋት ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።

6

 

ደብረብርሃን፡ ሚያዝያ 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የምርት ሂደትን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እና በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድን (ዶ.ር) ጨምሮ የክልል እና የዞን ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ እንደገለጹት ፋብሪካው ጥራት እና ብዛትን ያጣመረ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በስፋት በማቅረብ ላይ ይገኛል።

ፋብሪካው በቀን 17 ሺህ ቶን፣ በዓመት ደግሞ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን በላይ ሲሚንቶ የማምረት አቅም ያለው በመኾኑ፣ በሀገሪቱ የታየውን የሲሚንቶ እጥረት ለመቅረፍ እና የዋጋ መረጋጋት እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መኾኑን ገልጸዋል።

የፋብሪካው ልዩ መገለጫዎች ተብለው በጉብኝቱ ወቅት ከተጠቀሱት መካከልም፦

👉የአካባቢውን ጥሬ ዕቃ በስፋት ጥቅም ላይ በማዋል ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች ተምሳሌት መኾኑ

👉ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት የሰጠ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የብክለት መጠንን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ

👉 ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ መግባቱ ለሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ መነቃቃት ትልቅ ተስፋ መፍጠሩ ይጠቀሳል።

የክልሉ መሪዎች ፋብሪካው የሀገር በቀል ኢንዱስትሪዎችን አቅም በተግባር ያሳየ ግዙፍ ፕሮጀክት መኾኑን ገልጸው፤ ለቀጣይ ስኬታማ ጉዞው አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ፦ ብርቱካን ማሞ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ በሀገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፍ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል።