“ሰላማችንን እናጸናለን፤ ጥላቻን እናወግዛለን” የወፍላ፣ ኮረም እና ዛታ ሠልፈኞች

10

 

ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የወፍላ፣ የኮረም፣ የዛታ እና የአበርገሌ ተፈናቃዮች ራሱን ህወሃት እያለ የሚጠራውን ቡድን የጠብ አጫሪነት እና የትንኮሳ ድርጊት የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው። ሰልፈኞቹ ሰላም ወዳድነታቸውን እና ሀገር ባስቀመጠችው አቅጣጫ መሰረት ምርጫ ለማካሄድ ያላቸውን ጽኑ ዴሞክራሲያዊ እምነት በሰልፉ ላዬ አስተጋብተዋል። ሰላማቸውን እና ኑሯቸውን የሚያውክ ማኛውንም አካል እንደማይፈልጉም በሰልፉ አረጋግጠዋል። በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ የተለያዩ መልእክቶችን እያስተጋቡ ሲኾን ከነዚህ ውስጥም፦

👉እኛ የዛታ፣ የኮረም፣ የአበርገሌና የወፍላ ሕዝቦች ሰላማችን እናፀናለን፣ ጥላቻን እናወግዛለን!

👉ድምፃችን በጥይት አይታፈንም!

👉በወያኔና በተላላኪዎች ሴራ ሀገራዊ ምርጫችን አይደናቀፍም!

👉ማንነት የዴሞክራሲ ጉዳይ ሳይሆን የተፈጥሮና የሰብአዊ መብት መሆኑ ታውቆ፣ መብታችን እንዲከበርልን እንጠይቃለን።

👉ራሱን ህወሃት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኮረም፣ በወፍላና ዛታ የሚፈፅመውን የመሬት ወረራ እናወግዛለን የሚሉ ናቸው።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article” የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለትውልድ የሚሻገሩ ተግባራትን ሠርቷል” ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ
Next articleየኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸለመ።