መሬት አጥረው በሚያስቀምጡ እና ሼድን ለሌላ ዓላማ በሚጠቀሙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።

11

 

ደብረ ብርሃን: ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በደብረ ብርሃን ከተማ ”የኢትዮጵያ ታምርት” የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

በውይይቱ የተሳተፉ ባለሃብቶች አሁን ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በቀጣይ ኢንቨስትመንቱን ይበልጥ ለማሳደግ የደረቅ ወደብ ግንባታ እና የፍጥነት መንገድ እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል።

አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና የብድር አቅርቦት ላይ ያሉ ክፍተቶች እንዲታረሙላቸውም አንስተዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) ሼድ ገንብቶ ለታለመለት የኢንዱስትሪ ዓላማ ሳይኾን ለሌላ ተግባር ማዋል ሕገ ወጥነት በመኾኑ በፍጥነት ሊታረም እንደሚገባ ገልጸዋል።

ፋብሪካዎች የተቀመጠውን የአሠራር ሥርዓት ተከትለው የአካባቢ ብክለት እንዳይኖር መሥራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በገበያ ትስስር በኩል በርካታ ውጤቶች ቢመዘገቡም አሁንም ዘርፉን ይበልጥ ለማጠናከር ጠንካራ ሥራ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) “መሬት አጥረው በሚያስቀምጡ እና ሼድ ለሌላ ዓላማ በሚጠቀሙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ” አሳስበዋል።

ወደ ምርት ለመሸጋገር ለቀረቡት አልሚዎች ድጋፍ እንደሚደረግ እና ምርት ላይ ያሉትን ደግሞ የሚፈትኗቸውን ችግሮች እንደሚፈቱም አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ፦ ለዓለም ለይኩን

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleአባት አሠልጣኝ ልጅ ሠልጣኝ ኾነው የተገናኙበት ወታደራዊ ማሠልጠኛ
Next articleየምርምር ማዕከላት ማንሠራራት አለባቸው።