የምርምር ማዕከላት ማንሠራራት አለባቸው።

10

 

ደብረ ታቦር: ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አምስተኛው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

ጉባዔው “የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት እና ባሕል ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብቴ ዓለምነው (ዶ.ር) የጉባዔው ዓላማ ተቀዛቅዞ የቆየውን “የምርምር ማዕከል ለማንሠራራት እና ወደ ነበረበት ለመመለስ ነው” ብለዋል።

በምርምር፣ በማኅበረሰብ አገልግሎት፣ በባሕል እና በቴክኖሎጂ ሽግግር በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋልም ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው በደብረ ታቦር ሆስፒታል ከ100 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ታካሚዎች ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ በትኩረት እየሠራ እንደኾነም ገልጸዋል።

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ሕትመት እና ሥነ ምግባር ሥርጸት ዳይሬክተሩ መሠረት በላቸው (ዶ.ር) ከምርምር በመነሳት ወደ ማኅበረሰቡ ለመድረስ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ የሚረዳ ጉባዔ ነው ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጅ ሽግግር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተሩ ታደሰ ዋለልኝ (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው በአካባቢው ከሚገኙ ተቋማት እና ዓለም-አቀፍ ድርጅቶች ጋር የጋራ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረጉ ትስስሮችን በመፍጠር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሁለንተናዊ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ምሁራንም በምርምር ማዕከሉ የልምድ ልውውጥ በማደረግ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል እንደኾነ ገልጸዋል።

ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጥምረት መሥራት መቻል ውጤት እያመጣ ነውም ብለዋል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleመሬት አጥረው በሚያስቀምጡ እና ሼድን ለሌላ ዓላማ በሚጠቀሙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።
Next articleየሠራተኞችን መብት እና ደኅንነት ለማስጠበቅ እየተሠራ ነው።