🇪🇹”ሀገር ከሌለች እናት አትኖርም” እህትማማቾቹ የብር ሸለቆ ተመራቂዎች

35

 

ባሕርዳር፡ ሚያዝያ 23/2018ዐዓ.ም (አሚኮ) በብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩት እህትማማቾቹ ኦብሴ አብዱ እና ታሪኳ አብዱ ሥልጠናቸውን በስኬት አጠናቅቀው ለምረቃ በቅተዋል።

እህትማማቾቹ ከልጅነት ጀምሮ የወታደር ሙያ ምኞታቸው ነበር።

መሠረታዊ ወታደር ኦብሲ አብዱ እንደገለጸችው እናቷን ላለማስጨነቅ ከእህቷ ተነጥላ ብቻዋን ለመግባት መወሰኗን ታስታውሳለች። ነገር ግን ይህንን የሰማችው እህቷ ታሪኳ አብዱ ደም ከውኃ ይወፍራል፣ ሀገር ከራስ ይበልጣል እንደሚባለው አስገራሚ ውሳኔ ወሰነች።

“እህቴ ለሀገሯ ቆርጣ ስትወጣ እኔ እንዴት እቀራለሁ?” በማለት የእህቷን የሀገር ፍቅር መንገድ ተከትላለች። ይህቺ ጥያቄ ለሁለት እህትማማቾች ብቻ ሳይኾን ለሁላችንም የምታስተጋባ የሞራል ጥሪ ናት።

እናታቸው፣ ሁለቱንም ልጆቻቸውን ወደ ውትድርና መሸኘት ቀላል አልነበረም። አንዷ ከጎኔ ትሁን ቢሉም፣ ልጆቹ ግን ለአንድ እናት ሳይኾን ለሺዎች እናቶች መከታ ለመኾን መረጡ። “ሀገር ከሌለች እናት አትኖርም!” የሚለው መርህ በቤታቸው ሳይኾን በልባቸው የታተመ ዕውነት ኾነ።

ዛሬ በብር ሸለቆ የምረቃ ሜዳ ላይ፣ በወታደራዊ ሥነ-ምግባር የታነጹት ኦብሴ እና ታሪኳ “ለሰንደቅ ዓላማችን ክብር ማንኛውንም መስዋዕትነት እንከፍላለን” ሲሉ ቃል ገብተዋል። ውትድርና ሙያ ብቻ ሳይኾን ጥንካሬ፣ ወኔ እና የራስን ምቾት ለሀገር አሳልፎ መስጠት መኾኑን በተግባር አሳይተዋል።

እነዚህ እህትማማቾች ዛሬ ለኢትዮጵያ ሴቶች የጥንካሬ ምልክት፣ ለወጣቶች ደግሞ የሀገር ፍቅር ተምሳሌት ናቸው። ከአንድ ማህፀን ወጥተው ለአንድ ዓላማ በጋራ መቆም ከዚህ በላይ ምን ኩራት አለ? 🇪🇹

ዘጋቢ:-አሰፋ ልጥገበው

#አሚኮ #ኢትዮጵያ #ብርሸለቆ #የሀገርፍቅር #እህትማማቾች #EthiopianDefenseForce

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleለዜጎች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለማስተላለፍ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።
Next article“በጸጥታ ችግር ምክንያት የሚስተጓጎል የምርጫ ሂደት የለም” እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)