“አሚኮ ትላልቅ የሕዝብ አጀንዳዎችን ይዞ በትኩረት ሲሠራ ቆይቷል” ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ

19

ባሕርዳር፡ ሚያዝያ 21/2018ዐዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በበጀት ዓመቱ ያለፋት ዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ እንዳሉት ተቋሙ ባለፉ ዘጠኝ ወራት ትላልቅ የሕዝብ አጀንዳዎችን ይዞ በትኩረት ሲሠራ ቆይቷል። በቀጣይም የይዘትን ሥራ ውጤታማ በማድረግ ላይ ትኩረት እንደሚሰጥም ተናግረዋል። በየዘርፉ አሠራርን መፈተሽ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ዘገባዎችን ማድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅሰዋል።

ለዲጂታላይዜሽን ትኩረት መስጠት እና በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር በትኩረት መሥራትን ማስቀጠል ላይም ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አሥፈጻሚ ጋዜጠኛ ደረጀ ሞገስ የሚዲያ ስኬት በዕምነት ላይ እንደሚመሠረት እና አሚኮ ደግሞ ታማኝ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ እያደረሰ መኾኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ብዙ ዘገባ ከማምረት ባሻገር የዘገባ ጥራትን ማስጠበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

የሚሠሩ ሥራዎች ወጥነት እና ዘላቂነት ያላቸው እንዲኾኑ ትኩረት እንደሚደረግም ገልጸዋል። በትብብር ተቀናጅቶ መሥራት እና ቴክኖሎጅን ማሳደግም የተቋሙ ዋነኛ ተግባራት ኾነው ይቀጥላሉ ነው ያሉት።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ተቋሙ ባለፋ ዘጠኝ ወራት ለዲጅታል ሚዲያ ዘርፍ አዲስ መዋቅር በመፍጠር እና በጸጥታ ችግር ውስጥ ኹኖም ጥራት ያላቸውን ዘገባዎችን በሁሉም ቦታ እና በብዙ የሚዲያ አማራጮች ተደራሽ በማድረግ ጥሩ አፈጻጸም አስመዝግቧል ነው ያሉት።

የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በማቅረብ እና በመጠቀም ሥራን ቀልጣፋ ማድረግ እንደተቻለም ተጠቅሷል።

የዜና አቀራረብ ሥርዓትን ሳቢ እና ማራኪ ለማድረግ እንደተሠራም በመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስቷል። በተለያዩ አካባቢዎች ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ዘገባዎችን እና ፕሮግራሞችን በቀጥታ ሥርጭት ሽፋን መሥጠት እንደተቻለም ተጠቅሷል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ፕሮግራሞችን ሳቢ ለማድረግ ጥረት ማድረግ፣ ከጥቆማ ይልቅ የዕቅድ ዘገባን ማሳደግ እና የገቢ አፈጻጸምን ማሻሻል እንደተቻለም ተነስቷል።

ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ከራሴ ባሻገር ለሀገሬ ሕልም አለኝ” ባለ ራዕዩ ወጣት