“ኢትዮጵያ ትላንት ከነበራት አቅም የላቀ ደረጃ ላይ ትገኛለች” ጄኔራል አበባው ታደሰ

11
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ የደቡብ እዝን የዝግጁነት ደረጃ በግዳጅ ቀጣናው ተገኝተው ተመልክተዋል።
በሥፍራው ባስተላለፉት መልዕክት ደቡብ እዝ ማንኛውንም ግዳጅ በድል መፈጸም የሚያስችል አቅም ገንብቷል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ትላንት ከነበራት አቅም ይልቅ ዛሬ ላይ በሰው ኀይል እና በቴክኖሎጂ የተሻለ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል። ደቡብ እዝ በአስቸጋሪ መልክዓ ምድር ፈታኝ የውጊያ ሥልጠናዎችን በማድረግ የደረሰበት የዝግጁነት ደረጃ የሚደነቅ መኾኑንም ገልጸዋል።
የደቡብ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ደቡብ እዝ በተሰለፈበት የግዳጅ ቀጣና ሁሉ ኢትዮጵያን ከጀመረችው የልዕልና ጉዞ ለማደናቀፍ የሚደረጉ የጸረ ሠላም እንቅስቃሴዎችን እየመከተ እና እየደመሰሰ ሃገርን ማስቀጠል የቻለ አንጋፋ እዝ መኾኑን ተናግረዋል።
ከሀገር መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሠራዊቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ እና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ነው ብለዋል። በየትኛውም ተልዕኮ አኩሪ ድል ለማስመዝገብ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉንም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ኢትዮጵያ ከምናስበው በላይ እየተገነባች ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleየናፍጣ ነዳጅ የአቅርቦት መጠን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት በፊት ወደነበረበት እንዲመለስ ተደረገ።