
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ.ር) በተገኙበት ‘’የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ መልዕክት በማኅበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የሚቀርቡበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
ባለፉት ስምንት አመታት በተለይም በትምህርት፣ ጤና፣ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በባሕል፤ በኪነ-ጥበብ፣ ስፖርት፣ በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች የተመዘገቡ ውጤቶች በስፋት የተተነተኑበት መድረክ ነው።
የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ዘርፉ በለውጡ ዓመታት ያስመዘገበውን ስኬቶች አብራርተዋል።
ከለውጡ በፊት ለአደባባይ ክብረ በዓላት ትኩረት ማነስ፣ ባሕላዊ የፍትሕ እና ዳኝነት ሥርዓትን ያለመጠቀም፣ የአካታችነት ችግር እና የባሕል እሴቶችን ለአንድነት ያለመጠቀም ችግሮች እንደነበሩ ገልጸዋል።
የለውጡ መንግሥት ለነዚህ ክፍተቶች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ዘርፉ ወሳኝ ለውጦች እንዲያስመዘግብ መደላድል ፈጥሯል ነው ያሉት።
ከስኬቶቹም መካከል ለ83 ክብረ በዓላት እውቅና መስጠት እና መከበር፣ 36 አዲስ ባሕል ማዕከላት መገንባት፣ ዲጂታል የቅርስ መረጃ አያያዝ ሥርዓት መዘርጋት፣ የባሕል እና የብዝኃ ልሳን ፖሊሲ ትግበራ፣ ተጨማሪ ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኙ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች፣ በርካታ ቤተ መጻሕፍት ግንባታ እና የንባብ አገልግሎት መበራከት ብዝኃ ልሳን ፖሊሲ ትግበራና የሙያ ማኅበራት መደራጀት እና ዘርፉን ለዲፕሎማሲ ስኬት ከመጠቀም ባለፈ አደይ አበባን ጨምሮ 17 ሺህ 636 አዳዲስ ስታዲየሞች ግንባታ የዘርፉ ትልቅ እመርታዎች ናችው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
