
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ.ር) በተገኙበት ‘’የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ መልዕክት በማኅበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የሚቀርቡበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
ባለፉት ስምንት አመታት በተለይም በትምህርት፣ ጤና፣ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በባሕል፤ በኪነ-ጥበብ፣ ስፖርት፣ በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች የተመዘገቡ ውጤቶች በስፋት የተተነተኑበት መድረክ ነው።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በሥራ እና ክህሎት ዘርፍ በለውጡ ዓመታት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችውን ስኬቶች አብራርተዋል።
ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት በማድረግ፣ ብቁ የሰው ሀብት፣ ምቹ እና አስተማማኝ የሥራ ዕድል የተፈጠረባት ኢትዮጵያን ማየት የተለመው ይህ ዘርፍ ከለውጡ በኋላ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሥራ ስመሪት፣ ዜጎች በቤት ውስጥ እና ባሉበት ኾነው በሚሰሯቸው ሥራዎች አማካኝነት ለ19 ሚሊዮን 872 ሺህ 846 ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯል ብለዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ኢንተርፕርነር ተቋማትን በመፍጠር፣ ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ ሀገር ተቋማት ጋር አጋርነት በመፍጠር፣ የቢዝነስ መስፋፋት እና የልህቀት ማዕከላት በማሳደግ፣ ቲቬት ዲጂታላይዜሽን በማረጋገጥ ሰፊ ሥራዎች በመተግበራቸው ስኬት መገኘቱን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
