
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ.ር) በተገኙበት ‘’የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ መልዕክት በማኅበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የሚቀርቡበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
ባለፉት ስምንት አመታት በተለይም በትምህርት፣ ጤና፣ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በባሕል፤ በኪነ-ጥበብ፣ ስፖርት፣ በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች የተመዘገቡ ውጤቶች በስፋት የተተነተኑበት መድረክ ነው።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶችን አቅርበዋል። ዘርፉ ከለውጡ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት ካስመዘገባቸው ዋና ዋና ስኬቶች መካከል ለ30 ዓመታት የቆየው የጤና ፓሊሲን በመከለስ፣ መከላከል ከሚለው መርህ በተጨማሪ አክሞ የማዳን ቁርጠኛ የፖሊሲ አመራር፣ የተቋም ግንባታ፣ የጤና መሠረተ ልማት ለውጦች፣ መድኃኒት፣ ክትባት፣ የሕክምና ግብዓቶች ምርት አቅርቦት፣ ቁጥጥር ጭማሪ እና የጤና ፋይናንስ እመርታ ቁልፍ እና ዋነኞቹ የለውጥ ሥራዎች ናቸው ብለዋል።
የወረርሽኝ ልየታ እና ቁጥጥር፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ፣ የጤና ባለሙያዎችን ማብቃት እና ቁጥራቸውን ማሳደግ፤ የዲጂታል ጤና፣ በዘርፉ የተተገበሩ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ግንባር ቀደም ስኬቶቿ መኾናቸውን ገልጸዋል።
የጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ከፍ ያሉ እመርታዎች የተመዘገበበት አንዱ እና ዋነኛው መስክ መኾኑን ተናግረዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያ በተለያዩ መድረኮች ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመርጣ ድርድሮችን እና ንግግሮችን እንድትመራ አስችሏታል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
