የሆርሙዝን ወሽመጥ እንደ ፖለቲካዊ ግፊት መጠቀም አይገባም።

7

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እና የዓለም የንግድ መስመር የኾነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ ክፍት ለማድረግ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

የአልጀዚራ ዘገባ እንደሚያመላክተው የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጄድ አል አንሳሪ የሆርሙዝ መስመርን እንደ ፖለቲካዊ ግፊት መጠቀም እንደማይገባ ገልጸዋል። የባሕር ላይ ትራንስፖርትን ማገጃ ማድረግ በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ፍጥጫ ዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። በርካታ ሀገራት የውኃ መስመሩ በአስቸኳይ እና ያለ ምንም ገደብ እንዲከፈት ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የብሔራዊ ደኅንነት ቡድን ጦርነቱን ለማቆም የሆርሙዝ የውኃ ላይ መስመርን ለመክፈት እና የኒውክሌር ድርድሩን ለጊዜው ለማራዘም የሚያስችል የኢራንን የሰላም ዕቅድ እየመረመረ መኾኑን ገልጸዋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጊቺ በሴንት ፒተርስበርግ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ባደረጉት ውይይት ቴህራን ድርድሩን በድጋሚ ለመጀመር የቀረበላትን የአሜሪካ ጥያቄ እያጤነች መኾኑን ጠቁመዋል።

በስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleጥራቱን የጠበቀ እና ያልተቆራረጠ የመድኃኒት አቅርቦትን በማሳደግ የጤናው ዘርፍ እንዲጠናከር እየተሠራ ነው።
Next articleበጥናት በተደገፈ መልኩ የትምህርት ዘርፉን ፍላጎቶች እና ተግዳሮቶች በመለየት በመሥራቱ ውጤት ተገኝቷል።