የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ አዲስ አበባ ገቡ።

7

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በክብር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

‎የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማት እና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ሥራዎችን ቅድሚያ የሰጠ ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መኾኑም ተገልጿል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleበጎንደር ከተማ ሰው ለማገት እና ለመግደል ተዘጋጅተው የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።