በጎንደር ከተማ ሰው ለማገት እና ለመግደል ተዘጋጅተው የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

8

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር አንቻው ቀበሌ ውስጥ ሰው ለማገት እና ለመግደል ተዘጋጅተው የነበሩ አምስት የጽንፈኛ ቡድን አባላት በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከተማ አሥተዳደሩ አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ከኅብረተሰቡ በተገኘ ጥቆማ መሰረት በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተሰብስበው እያሉ በፖሊስ እና በሌሎች የጸጥታ አካላት በተቀናጀ እርምጃ መያዛቸው ተገልጿል።

በእርምጃው የተያዙት ተጠርጣሪዎች ባበይ (የሽዋስ) አየነው፣ አማኑኤል አስረስ ባንቲሁን፣ ሀብቱ ክብርነው አወቀ፣ ገብረ መስቀል ንጉሤ ሰማ እና አሰፋ ማሩ የተባሉ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ ጋር የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና በርካታ ጥይቶች መያዛቸው ተገልጿል።

ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ባበይ (የሽዋስ) አየነው የተባለው ግለሰብ በላይ አርማጭሆ ወረዳ ሰው በመግደል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተሰጠበት መኾኑ ተመላክቷል።

ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ጥብቅ ምርመራ እያካሄደ መኾኑ ተገልጿል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleከይለፍ-ቃል ወደ ማለፊያ-ቁልፍ…
Next articleየሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ አዲስ አበባ ገቡ።