ከይለፍ-ቃል ወደ ማለፊያ-ቁልፍ…

6

 

ባሕርዳር፡ ሚያዚያ 19/2018ዓ.ም (አሚኮ)የእንግሊዝ ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕከል ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃልን (Password) በመተው በጣት አሻራ ወይም በፊት ምስል ወደ ሚሠሩ የይለፍ ቁልፎች (Passkeys) እንዲሸጋገሩ እያሳሰበ ነው። ይህም ይበልጥ አስተማማኝ እንደኾነ እያሳሰቡ ነው።

ይህ የጥበቃ ዘዴ በአኹኑ ወቅት እንደ አፕል፣ ጎግል እና ኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ባሉ ትልልቅ ድርጅቶች ድጋፍ ተቀባይ እያገኘ ነው ተብሏል።

የኢንፎርሜሽን ደህንነት አሥተሥተዳደር በፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው በኢትዮጵያ የዲጂታል እንቅስቃሴ እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የሳይበር ጥቃቶች እየጨመሩ ነው።

ይህን ችግር የይለፍ ቁልፎችን መጠቀም የደህንነት ጥበቃን ለማጠናከር ይረዳል ተብሏል። ይኹን እንጂ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንደሚያስጠነቅቁት ይህ ቴክኖሎጂ ገና በሁሉም ድረ-ገጾች እና መተግበሪያዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ስላልተተገበረ ብቻውን የመጨረሻ መፍትሄ ሊኾን እንደማይችል ተጠቁሟል።

በጣት አሻራ ወይም በፊት ምስል ወደ ሚሠሩ የይለፍ ቁልፎች በማይደገፉባቸው የዲጂታል መድረኮች ላይ አኹንም ጠንካራ የይለፍ ቃላትን፣ የይለፍ-ቃል አሥተዳዳሪዎችን (Password Managers) እና ባለብዙ-ደረጃ ማረጋገጫን (Multi-factor Authentication/2FA) መጠቀም ወሳኝ የሳይበር ደህንነት ልምድ ነው ተብሏል።

ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleቀድሞ እርሻ መጀመር ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ አለው።
Next articleበጎንደር ከተማ ሰው ለማገት እና ለመግደል ተዘጋጅተው የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።