
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ 12ኛውን የግብርና ልማት አጋር አካላት የግንኙነት አማካሪ ካውንስል ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ደረጀ ማንደፍሮ ጉባኤው በ12ኛው ጉባኤ ሲመክር ባለፈው ዓመት በተካሄደው ጉባኤ ምክረሀሳብ የተሰጠባቸው እና ጸድቀው ለምርምር የተሰጡ የቤት ሥራዎች መተግበር ወይም አለመተግበራቸው ውይይት እንደሚያደርግባቸው ተናግረዋል።
ኀላፊው አርሶአደሮች ምን እንደሚያለሙ ብቻ ሳይኾን ለምን እና ለማን እንደሚያለሙ ጭምር ግንዛቤ ማስያዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በዘንድሮው ጉባኤ ላይ የሚነሱ ጉዳዮች እና ምክክሮችም ከንግግር አልፈው በተግባር በአርሶአደሮች ሕይወት ላይ የሚተገበሩ መኾን እንዳለባቸውም አንስተዋል። “የግብርና ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎች ሥራ አርሶአደሮቹ ደጅ ላይ መኾን አለበት ነው ያሉት።
የዚህ ዓመት ጉባኤ ካለፋ ጉባኤዎች ለየት ባለ መንገድ ክልሉ ከነበረበት የግብርና ሥራዎች ችግር ለመውጣት በተያዘው በጀት ዓመት የአምስት ዓመት የአሻጋሪ ዕድገት እና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ፍኖተ ካርታ መተግበር የጀመረበት በመኾኑ በአጽንኦት የሚመከርበት ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
