የቅድመ ምርጫ ተግባራትን ተከትሎ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሠራጩ ነው።

5

 

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማከናወን ላይ ያለውን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ-ምርጫ ተግባራትን ተከትሎ በርካታ ሀሰተኛ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችና ዜናዎች መፈጠራቸውን ገልጿል።

ቦርዱ አሳሳች መረጃዎችን የሚያሠራጩ ግለሰቦችን ተጠያቂ አድርጋለሁም ብሏል። ማኅበረሰቡም ቦርዱን ከተመለከቱ ሀሰተኛ ዜናዎች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።

የተረጋገጡ የቦርዱን ዜናዎች እና ማስታወቂያዎች ከ438,000 በላይ ተከታይ ባለው ይፋዊ የቦርዱ የፌስቡክ ገጽ እና በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር አማራጮች እንዲከታተልም ጥሪ አቅርቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ማያርድት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ።
Next articleየንጹሕ መጠጥ ውኃ ተደራሽነትን ለማስፋት በትኩረት እየተሠራ ነው።