የንጹሕ መጠጥ ውኃ ተደራሽነትን ለማስፋት በትኩረት እየተሠራ ነው።

4

 

ከሚሴ: ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አምስተኛው የአማራ ክልል የከተሞች የመጠጥ ውኃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ድርጅቶች መደበኛ ጉባኤ በከሚሴ ከተማ ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ አማካሪ ወልደ ትንሣኤ መኮንን (ዶ.ር) የንጹሕ መጠጥ ውኃን ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በዘመናዊ መንገድ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የውኃ ብክነትን በመቀነስ ዘላቂ የውኃ አጠቃቀም እና አሥተዳደር ሥርዓት እንዲኖር በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

የአማራ ክልል የከተሞች መጠጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅቶች ማኅበራት ፕሬዝዳንት ይርጋ ዓለሙ የከተሞችን ውኃ ጥራት እና ተደራሽነት ለማሻሻል የተሠሩ ሥራዎች ውጤት እንዳስመዘገቡ ገልጸዋል።

የውኃ ማኅበራትን ወደ ፌዴሬሽን በማሳደግ እና ችግሮችን በመለየት ለተግባራዊነቱ በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም ከተማ አሥተዳደሩ ንጹሕ መጠጥ ውኃን በማቅረብ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ንጹሕ መጠጥ ውኃን ለማኅበረሰቡ ለማቅረብ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። የማኅበረሰቡ ተሳትፎም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየቅድመ ምርጫ ተግባራትን ተከትሎ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሠራጩ ነው።