“በቀጣይ ጠንካራ ሕግ የማስከበር ሥራ ይከናወናል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

6

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገሙ ነው።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በቀሪ ወራቶች ጉድለቶችን በመለየት እና በማረም ተግባራትን በትኩረት መፈጸም እንደሚገባ ገልጸዋል።

ከባለፉት ጊዚያት በተለየ መልኩ ሰላምን ለማስከበር ክልሉ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በአስቸጋሪ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ ኾነን የምርጫ ሂደቱን ለማሥፈጸም እየሠራን ነው ብለዋል። የሕዝብን አቅም በመጠቀም መሥራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ሕግ የማስከበር ተግባራትን እና የምርጫ ሥራዎችን በቅንጅት እና በጥራት መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። “በቀጣይ ጠንካራ ሕግን የማስከበር ሥራ ይከናወናል” ነው ያሉት።

የትኩረት መስኩን የተገነዘበ፣ ተልዕኮን ተቀብሎ ሁሉን አቀፍ ውጤታማነት የሚፈጥር እና ሥራን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ የሚፈጽም መሪ ለመገንባት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ፓርቲው ያከናወናቸውን ተግባራት፤ የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም፤ የሰላም እና የልማት ሥራዎች፤ ማኅበረሰብ ተኮር የኾነ ሕግ የማስከበር ሥራና በገጠር ልማት ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት የመድረኩ ትኩረቶች ናቸው።

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የዘጠኝ ወራት አፈጻጸምን እየገመገሙ ነው።
Next article“የክልሉ አንጻራዊ ሰላም የመጣው ለሕዝብ መስዋዕትነት በከፈሉ ጀግኖች ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ