ሰው ተኮር የኾኑ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

14
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሐረሪ ክልል የአሥፈጻሚ አካላት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማን እያካሄደ ነው።
የሐረሪ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ግምገማው በየዘርፉ የተቀመጡ ዕቅዶችን አፈጻጸም በመፈተሽ ለቀጣይ ተግባራት ራስን ከማዘጋጀት ባለፈ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ብለዋል።
አፈጻጸሙን ከዕቅዱ አንጻር መፈተሽ እና ውስንነቶችን ለይቶ በቀሪ ሦስት ወራት መፈጸም እንደሚገባም አንስተዋል።
በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን መፈተሽ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ቱሪዝም፣ ኢንቨስትመንት እና ሌሎች ዘርፎች ለክልሉ ኢኮኖሚ እድገት እያበረከቱት የሚገኘውን አስተዋጽኦ መመልከት እንደሚገባም ገልጸዋል።
የግብርና ምርት እና ምርታማነትን ለማጎልበት የተሠሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት።
የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፤ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን ለማስወገድ የተከናወኑ ተግባራትን በጥልቀት መመልከት የግምገማው አንዱ ዓላማ ነው ብለዋል።
ከሐረሪ ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሰው ተኮር የኾኑ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleተማሪዎችን ማብቃት የነገ ሀገርን መገንባት ነው።
Next articleበሳይንስ እና ፈጠራ የተጀመሩ ተግባራት እያደጉ ሲሄዱ የበለጸገ ትውልድን ማፍራት ይቻላል።