ዛሬ ሥራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት በውስጡ ምን ይዟል ?

10

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ዛሬ ሥራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት አስፈላጊ የኾኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለት እና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ኾኖ የተዘጋጀ ነው። ቀልጣፋ እና አስተማማኝ አሠራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እና ሥርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ ነው።

‎አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ስርዓት ያለው ነው። የተለያዩ የክፍያ አማራጮችንም አካቷል። ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ኃይል በከፊል ከ8 ኪሎ ዋት የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝ ነው። አስተማማኝ ኢንተርኔትም ተገጥሞለታል።

‎ በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡን ደህንነት እና ግልፅነትን ለመከታተል ካሜራዎች ተገጥመውለታል። መፍትሔ አምጪ ኾኖ የተዘጋጀው የፈጠራ ውጤት እና ተንቀሳቃሽ ክፍል፤ ከስምንት የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሚከተሉትን ወሳኝ አገልግሎቶች ይሰጣል።

‎👉 አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መስጠት
‎👉 የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ
‎👉 ለመንጃ ፈቃድ የሚያስፈልግ የሕክምና ምርመራ ማድረግ
‎👉የነዋሪነት መታወቂያ ማደስና የልደት ምዝገባ
‎👉የመንጃ ፈቃድ መስጠትና የተሽከርካሪ ታርጋ ማደስ
‎👉የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የመንገድ ፈንድ ክፍያን ማከናወን
‎👉 የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባና የመረጃ እርማት
‎👉 በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የሚሰጥ የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

‎ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ይህ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ ቀልጣፋ እና ተደራሽ የኾነ መፍትሔ ይሰጣል ተብሏል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleመገናኛ ብዙኀን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር በኩል ሊሠሩ ይገባል።
Next article“የመምረጥ እና የመመረጥ መብትን መጠቀም ከኢትዮጵያዊ ሁሉ ይጠበቃል” የሃይማኖት አባቶች