
ሰቆጣ: ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የመራጮች ምዝገባ የመጨረሻው ቀን ላይ ትገኛለች።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችም ካርድ ለማውጣት እየተመዘገቡ ነው።
መጋቤ ሥርዓት ቀሲስ ያሬድ ደሳለኝ በመጋቢት ወር መጀመሪያ ካርድ እንዳወጡ ነግረውናል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ካርድ በማውጣት ሀገራዊ ኀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የትኛውም ሃይማኖት የሀገርን ሕገ መንግሥት አይቃወምም ያሉት ደግሞ ሃጂ መሐመድ አደም ናቸው። ሕገ መንግሥቱ የሰጠንን “የመምረጥ እና የመመረጥ መብት መጠቀም ደግሞ ከኢትዮጵያዊ ሁሉ ይጠበቃል” ነው ያሉት።
በተለያዩ ምክንያቶች ካርድ ያላወጡ ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ የሃይማኖት አባቶቹ ገልጸዋል።
የመራጮች ምዝገባ ተራዝሞ መቆየቱ በተለያዩ ምክንያቶች ካርድ ላላወጡ እናቶች ትልቅ ዕድል ኾኖልናል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ገነት ግርማ እና ወይዘሮ ወርቅ መኮነን ናቸው።
ዘጋቢ፦ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
