የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ጋር ተወያዩ።

23

 

ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል።

አምባሳደሩ በቆይታቸው የጤና ተቋማትን፣ ትምህርት እና በከተማዋ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን እንደሚመለከቱ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከ120 ዓመታት የላቀ በመከባበር እና በትብብር ላይ የተመሠረተ የዲፕሎማሲ ታሪክ ያላቸው ሀገራት ናቸው።

አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በባሕር ዳር በተደረገላቸው አቀባበል መደስደሰታቸውን ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🚫ለጥንቃቄ!
Next articleሰው ሠራሽ አስተውሎት የትንበያ ሥራዎችን ወደ አዲስ ምዕራፍ የማሸጋገር ተስፋ ተጥሎበታል።