🚫ለጥንቃቄ!

105

 

የባንክ ሂሳብን ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰርን በተመለከተ፦

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሁሉም ባንክ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሂሳባቸውን ከፋይዳ ቁጥር (ብሔራዊ መታወቂያ) ጋር ማስተሳሰር እና ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል።

አስከተጠቀሰው ጊዜ ድረስ የባንክ ሂሳብን ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ግድ የሚላቸው ቀጥለው በተዘረዘሩ ከተሞች የሚገኙ የሁሉም ባንክ ደንበኞች መኾናቸውን ኢቢሲ አስነብቧል።

-ባህር ዳር
-ጎንደር
-ደሴ
-ደብረ ብርሃን
-ኮምቦልቻ
-አዲስ አበባ
-ሀረሪ
-ድሬዳዋ አስተዳደር
-ሀዋሳ
-አርባ ምንጭ
-ወላይታ ሶዶ
-ሆሳዕና
-ወራቤ
-ቡታጅራ
-ወልቂጤ
-ሸገር
-ጅማ
-አዳማ
-ሻሸመኔ
-ቢሾፍቱ
-ባቱ
-አምቦ
-መቐለ
-አክሱም
-ዓዲግራት
-ጋምቤላ ከተማ እና
-አሶሳ ናቸው።

#በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፍ ደንበኞች ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማጠናቀቅ አለባቸው ተብሏል።

#ይሄን በማያደርጉት ላይስ?

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሂሳባቸውን የማያስተሳስሩ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው ከወጪ ወይም ተቀናሽ ግብይት የታገደ (No Debit) ይኾናል።

እገዳው የሚነሳው ደንበኛው የፋይዳ መታወቂያ ቁጥሩን ከባንክ ሂሳብ ቁጥሩ ጋር ሲያስተሳስር ብቻ ይኾናል።

#የተሰጠው አቅጣጫ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብን እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ነዋሪዎችን አይመለከትም።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለችግሮቻችን መፍትሔ ማድረግ ይገባል።
Next articleየአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ጋር ተወያዩ።