የባዮሜትሪክ ማንነት ማረጋገጫ ምንድን ነው?

6
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባዮሜትሪክ ማንነት ማረጋገጫ አንድ ሰው ከመወለዱ ጀምሮ ካሉት ተፈጥሯዊ መለያዎች ጋር የሚያስተሳስር እና ከሌላው ግለሰብ የሚለይበት አስተማማኝ መንገድ ነው።
በኢትዮጵያ በብሔራዊ የመታወቂያ ፕሮግራም አማካኝነት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽሕፈት ቤት የምዝገባ አሥተባባሪ ደጀኔ ገብሬ የባዮሜትሪክ ማንነት አንድ ሰው ከመወለዱ ጀምሮ ካሉት ተፈጥሯዊ መለያዎች ጋር የሚያስተሳስር እና ከሌላው ግለሰብ በልዩ ኹኔታ የሚለይበት አስተማማኝ መንገድ መኾኑን ጠቅሰዋል።
አሠራሩ በዋናነት እንደ እጅ አሻራ፣ የዓይን ብሌን እና የፊት ገጽታ ያሉ የባዮሎጂካል መለያዎችን መሠረት በማድረግ የሚሠራ ነው።
የ”ፋይዳ” መታወቂያ እነዚህን መረጃዎች ከግለሰቡ ሥነ ሕዝባዊ መረጃዎች ጋር በማጣመር ግለሰቡ በአንድ መለያ ቁጥር ብቻ እንዲታወቅ ያደርገዋል።
ይህ ሂደት አንድ ሰው በራሱ ማንነት ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረው ያስችላል። ማንነትን በማጭበርበር የሚፈጸሙ ድብቅ ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ለመግታትም ትልቅ ፋይዳ አለው።
ሌላው የዚህ ቴክኖሎጅ ፋይዳ ​ አገልግሎትን ማቀላጠፍ እና ለዜጎች ምቹ ኹኔታን መፍጠር ነው። ግለሰቦች የተለያዩ ሰነዶችን መያዝ ሳይጠበቅባቸው በአካላዊ አሻራቸው ብቻ ማንነታቸውን አረጋግጠው አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
ይህም በተመሳሳይ ፎቶ ወይም ሥም አማካኝነት በፋይናንስ እና በሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ የሚስተዋሉ ማጭበርበሮችን እና ሥርቆቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ያግዛል።
ቴክኖሎጂው ለአንድ ጊዜ ብቻ ከሚያገለግል የይለፍ ቃል (OTP) የዲጂታል ማረጋገጫዎች በበለጠ ፈጣን እና አስተማማኝ መኾኑንም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበወልቂጤ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን የሚደገፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ከአውሮፓ ኅብረት የዓለምአቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲከላ ጋር ተወያዩ።