በወልቂጤ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን የሚደገፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

8
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በድጋፍ ሰልፉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር “በሚል መሪ መልዕክት እየተካሔደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ ያለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት ስኬቶችን የሚዘክሩ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።
ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በድጋፍ ሰልፉ ከዕዳ ወደ ምንዳ የተሻገረ ኢኮኖሚ፣ ትላንትን ማከም ነገን መተለም፣ የጸና ሰላም፣ የተቃና ስርዓት፣ ከገጠር የተሰናሰለ ከተሜነት የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleየልማት ዕቅድ ማስፈጸሚያ ኢንሼቲቮችን በመለየት መተግበር
Next articleየባዮሜትሪክ ማንነት ማረጋገጫ ምንድን ነው?