የልማት ዕቅድ ማስፈጸሚያ ኢንሼቲቮችን በመለየት መተግበር

9
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከ100 ቀናት ሪፖርት እና ከ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ሥር የተቀረጹት ስድስት ታላላቅ ውጥኖች በመላ ሀገሪቱ የሚታይ ለውጥ እያመጡ ይገኛሉ።
👉 አረንጓዴ ዐሻራ፦ የሀገሪቱ የደን ሽፋን 23 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል። በዚህም የአርሶ አደሮች ገቢ እያደገ፣ አረንጓዴ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠሩ፣ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎች እየተከናወኑ፣ ሥነ-ምህዳሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጤናማ እየኾነ መጥቷል።
👉 ሀገራዊ የስንዴ ልማት፦ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና ሉዓላዊነትን እያረጋገጠች ትገኛለች። አዳዲስ የግብርና ዕውቀቶች እየተስፋፉ፣ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ግብዓቶችን እያገኙ፣ ውድ የኾኑ የውጭ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የሥራ ዕድሎች እየሰፉ እና የአርሶ አደሮች ገቢ እየጨመረ ይገኛል።
👉 የሌማት ትሩፋት፦ የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት እና ምርታማነት እየጨመረ ነው። የተመጣጠነ ምግብ በቀላሉና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኝ ከማድረግ ባለፈ፣ አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡና አካባቢው ይበልጥ እንዲጠበቅ እያደረገ ይገኛል።
👉 ዲጂታል ኢትዮጵያ፦ የሕግ፣ የፋይናንስ እና የማንነት መታወቂያ (ID) ሥርዓቶች ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ነው። የኢንተርኔት ተደራሽነትና የኦንላይን አገልግሎቶች እየተስፋፉ፣ የሞባይል ክፍያ ሥርዓት እየተጠናከረ እና የኢ-ኮሜርስ ንግድ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ እያተረፈ ነው።
👉 የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት፦ የከተሞች መሠረተ ልማት በአረንጓዴ ትራንስፖርት እየዘመነ ነው። ይህም የዜጎችን የኑሮ ጥራት እያሻሻለ፣ የአካባቢ ንግድን እያነቃቃ እና በከተማና በገጠር መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ ይገኛል።
👉 ኢትዮጵያ ታምርት፦ የማምረት አቅምና የምርቶች እሴት የመጨመር ሂደት እየተሻሻለ ነው። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እያደገ፣ የግብዓት አቅርቦት እየተጠናከረና አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠሩ ነው።
‎ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው እያንዳንዱ ምሰሶ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር፣ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article“የልማት ሥራው የነገዋን ኢትዮጵያ ብልጽግና የሚያበስር ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleበወልቂጤ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን የሚደገፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።