
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 13/2018 (አሚኮ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ባሕርዳር ገብተዋል።
አምባሳደሩ ባሕርዳር ሲገቡ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አምባሳደሩ በባሕርዳር በሚኖራቸው ቆይታ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
አምባሳደሩ የአሜሪካ መንግሥት ኢኒሼቲቮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል። በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎች ጉዳዮች ይወያያሉ ነው የተባለው።
የአምባሳደሩ ጉብኝት አሜሪካ በአማራ ክልል ለሰላም፣ ለልማት እና ብልጽግና ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከ120 ዓመታት የላቀ በመከባበር እና በትብብር ላይ የተመሠረተ የዲፕሎማሲ ታሪክ ያላቸው ሀገራት ናቸው።
የረጅም ጊዜ አጋርነት ያላቸው ሀገራቱ በዓለም አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በቀጣናው ጉዳዮች ላይ በጋራ ይሠራሉ።
በመከባበር እና በትብብር ላይ በተመሠረተው ግንኙነት የሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብሩ በርካታ ጉዳዮች ላይም በጋራ ሠርተዋል። አሁንም እየሠሩ ይገኛሉ።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
