
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ማሽኖች ወይም ኮምፒውተሮች እንደ ሰው የማሰብ፣ የመማር፣ ችግሮችን የመፍታት እና ቋንቋን የመረዳት ብቃት እንዲኖራቸው ተደርገው የሚሠሩበት የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው።
ከባሕላዊው የኮምፒውተር አሠራር የሚለየው ቀድሞ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ብቻ ከመፈጸም ይልቅ በሚሠበስቡት መረጃ ራሳቸውን እያሻሻሉ መሄዳቸው ነው።
#ጥቅሙ
የሰውን ልጅ ድካም እና ግድፈት በማስቀረት ሥራዎች በትክክል እንዲከናወኑ ያደርጋል።
መረጃዎችን በፍጥነት በመተንተን የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ይረዳል።
በአጠቃላይ ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴን እያቃለለ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ፈጣን የዲጂታል ሽግግር ላይ ባሉ ሀገራት ሥጋቶቹን ቀድሞ በመረዳት እና ራስን በዕውቀት በማዘጋጀት በጥንቃቄ መጠቀም ግን ግድ ይላል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
