የኒውክሌር ባለቤትነት መብቷን አሜሪካ ልትነጥቃት እንደማትችል ኢራን አስታወቀች።

3

 

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 11/2018 (አሚኮ) በመካከለኛው ምሥራቅ ለተፈጠረው ጦርነት በምክንያትነት በሚጠቀሰው የኒውክሌር ጉዳይ ዋሽንግተን እና ቴህራን ያላቸው አለመግባባት አሁንም እንደቀጠለ ነው።

የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን እንደዘገቡት ኢራን የኒውክለር ባለቤትነት መብቷን አሜሪካ ልትነጥቃት እንደማትችል አስታውቃለች።

አልጀዚራ እንደዘገበው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን ከኒውክሌር መብቷ የሚያግዱበት ምንም ዓይነት ምክንያት የላቸውም ሲሉ የኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ገልጸዋል።

“የትኛውንም ሀገር ለመውረር አንፈልግም፤ ሕጋዊ መብታችንን እና ፕሮጀክታችንን የምንጠቀመው ራሳችንን ለመከላከል ነው” ብለዋል የኢራኑ ፕሬዚዳንት።

“ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር መብቶቿን መጠቀም አትችልም ይላሉ፤ ነገር ግን ለምን ይህን እንደሚሉ ምክንያታቸውን አይናገሩም። የአንድን ሀገር መብት ለመንጠቅ እነሱ ማናቸው?” ሲሉ ፔዘሽኪያን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

በአሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleታዳሽ ኃይል በአርሶ አደሩ ቤት