ዜጎች በቀሪ ቀናት ካርድ በማውጣት የመራጭነት መብታቸውን መጠቀም አለባቸው።

25

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር በ2018 ዓ.ም የሚካሄደውን 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ የምዝገባ ሂደትን በተመለከተ ግምገማዊ መድረክ አካሂዷል።

በሂደቱም መልካም አፈጻጸሞችንና በቀጣይ መስተካከል ያለባቸውን ውስንነቶች ለይቶ በቀጣይ አራት ቀናት በንቅናቄ ወደሥራ በመግባት መመዝገብ ያለበትን መራጭ ለማስመዝገብ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

ካርድ ያላወጡ ዜጎችም በቀሪ ቀናት ውስጥ ካርድ በማውጣት የመራጭነት መብታቸውን መጠቀም እንዳለባቸው ተመላክቷል።

የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም ሙሀመድ (ዶ.ር)፣ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ፣ የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ደስታ አስራቴ እና ባለድረሻ አካላት በተገኙበት ነው ግምገማዊ መድረኩ የተካሄደው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመቃወምም ኾነ መደገፍ የሚቻለው በምርጫ ካርድ ነው።
Next articleየበቆሎ መስኖ ሥራችን ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)