ከ50 በላይ ሀገራት በያዝነው ዓመት ምርጫ እንደሚያካሂዱ መረጃ አለዎት?

2
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር 2026 ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 በላይ የተለያዩ የዓለም ሀገራት በተለያዩ ደረጃዎች ምርጫ ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዓለም አቀፍ የምርጫ ሥርዓቶች ፋውንዴሽን (IFES) በመባል የሚታወቀው እና በኢትዮጵያም ኾነ በሌሎች የዓለም ሀገራት የምርጫ ሂደቶች ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻ እና ፍትሐዊ እንዲኾኑ ድጋፍ የሚሰጥ መንግሥታዊ ያልኾነ ተቋም በርካታ ሀገራት በዚህ ዓመት ምርጫ ያካሂዳሉ ብሏል።
ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ፣ ዩጋንዳ የፕሬዝዳንት እና የፓርላማ ምርጫ፣ ጅቡቲ የፕሬዝዳንት ምርጫ፣ ዛምቢያ አጠቃላይ ምርጫ፣ ደቡብ ሱዳን ለመጀመሪያ ጊዜ አጠቃላይ ምርጫ እና ጋምቢያ የፕሬዝዳንት ምርጫ ያካሂዳሉ ብሏል ተቋሙ።
በሌሎች አሕጉራት ደግሞ አሜሪካ የኮንግረስ ግማሽ ዘመን ምርጫ፣ ብራዚል አጠቃላይ ምርጫ፣ ጣሊያን የሕገ-መንግሥት ሪፈረንደም ምርጫ፣ ጃፓን የተወካዮች ምክር ቤት፣ ሩሲያ የፓርላማ (ዱማ) ምርጫ እና ስዊድን አጠቃላይ ምርጫ እንደሚያካሂዱም መረጃው አካቷል።
ቤኒን የፕሬዝዳንት፣ ኮሎምቢያ የፕሬዝዳንት፣ ደቡብ ኮሪያ የአካባቢ መሥተዳድር እና ኒውዚላንድ የፓርላማ ምርጫዎችን እንደሚያካሂዱም ጠቅሷል።
እነዚህ የሚካሄዱ ምርጫዎች በዓለም አቀፍ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በዓለም የመጻኢ እጣ ፈንታ እና የፖለቲካ ሁኔታዎች ላይስ ለውጥ ያመጡ ይኾን?
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ለማስረከብ መስማማቷን ተናገሩ።
Next article“ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት የለውጥ ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር ሚናው የጎላ ነው” አቶ ዓለምአንተ አግደው