ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ለማስረከብ መስማማቷን ተናገሩ።

13
ባሕር ዳር ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢራን ያበለጸገችው ዩራኒየም ከአሜሪካ ጋር ለምታደርገው የሰላም ድርድር አንዱ እና ዋነኛው አላስማማ ያለ ጉዳይ ነው።
ባለፈው ዓመት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ያደረጉትን ጦርነት ጨምሮ ከሰሞኑ የሚስተዋለውን የተራዘመ ግጭት ያስነሳውም ይሄው የኒውክሌር ጉዳይ መኾኑ አይዘነጋም።
ንግግሮች ቢደረጉም ዘላቂ ሰላምን ሳያስገኙ ከአንዴም ሁለቴ ተበትነዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ የአሜሪካን ምጣኔ ሃብት በተመለከተው ጉባኤ ላይ ተገኝተው ስለሁለቱ ሀገራት ስምምነት ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት በቀጣይም ድርድሮች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል።
ቀጣዩ የሁለቱ ሀገራት የሰላም ድርድር እልባት የሚያስገኝ እንደሚኾንም ትራንፕ በእርግጠኝነት መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ልታስረክብ፣ የሰላም ስምምነቱም ሊፈጸም ከዳር ደርሰናል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየምርጫ ካርድ መውሰድ ከአካባቢ መጻዒ የልማት ዕድል ጋር የተያያዘ ነው።
Next articleከ50 በላይ ሀገራት በያዝነው ዓመት ምርጫ እንደሚያካሂዱ መረጃ አለዎት?