🇪🇹”በባንዲራው አምላክ ሰላማችን ይከበር” የቢቸና እና የእነማይ ነዋሪዎች

11

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያውያን ሕግ አክባሪ፣ ባለታሪክ እና የራሳችን እሴት ያለው ሕዝብ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ነፍጥ አንግበው ጫካ የሚገቡ ኃይሎች ማኅበረሰቡን የማይመጥኑ፣ ሰብዓዊነት የጎደላቸው ድርጊቶች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ የየአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

ዜጎች እየታፈኑ ከፍተኛ ገንዘብ እየተጠየቀባቸው መክፈል ያልቻሉ ደግሞ እንግልት እንደሚደርስባቸው በየጊዜው ይሰማል።

ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን ያልጠቀሱት የእነማይ ወረዳ ነዋሪ የኾኑት እማኝ እንደገለጹት ሻይ እና ሙዝ እየሸጡ ያሳደጉት ልጃቸውን በጫካ ያሉት ኀይሎች አፍነው ወስደው 600 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ይጠይቋታል። ነገር ግን መክፈል እንደማይችሉ ሲናገሩ ልጃቸው ተገድሎባቸዋል። “ሰላም ይስፈን፤ ሕዝብም እፎይታ ያግኝ” ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው የእነማይ ወረዳ ነዋሪ እንደገለጹት በጫካ ያሉት ኀይሎች በየቀኑ የገንዘብ መዋጮ እየጣሉብን ሰልችቶናል ይላሉ። “ይህንን ማድረግ ያልቻለ ቀን ይታሠራል፣ ማታ ይገረፋል” በማለት በምሬት ይናገራሉ።

ወላድ እናቶች በቤት እንዲወልዱ እና የከፋ ችግር እንዲደርስባቸው የፈረዱ ታጣቂዎች በየጊዜው አምቡላንስ ሳይቀር እንደሚያቃጥሉ ነው ነዋሪዎች የገለጹት። ከዚህ በላይ ሕዝቡ ምን እስከሚኾን ነው የምንጠብቅ በማለትም አብዝተው ይጠይቃሉ።

“ግፍ እየተፈጸመ ቆይቷል፣ በባንዲራው አምላክ ሰላማችን ይከበርልን” ብለዋል ነዋሪዎች በቆየው ባሕላቸው።

🔑መፍትሔው ምን ይሁን

📢 ሁሉም በየሃይማኖቱ የሕዝብን ሰላም የሚያውኩ ድርጊቶችን እና አስተሳሰቦችን ያውግዝ፣ ይምከር። ወደጫካ የወጡት ኃይሎች ይመለሱ እና ችግሮች በውይይት ይፈቱ በማለት ሕዝቡ እየተማጸነ ነው፤ መንግሥትም እያደረገ ያለውን የሰላም አማራጭ እንዲቀጥል ነዋሪዎቹ ሀሳባቸውን አንስተዋል።

🧑‍⚖️ የሕዝብን እና የመንግሥትን የሰላም ጥሪ አልቀበል ባሉት ላይ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድም ነው ነዋሪዎች የጠየቁት።

#ሰላም #አማራ #ኢትዮጵያ #አሚኮ #ወቅታዊ #ዜና

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዲፕፌክ (Deepfake) ምንድን ነው?
Next articleየመንግሥት ሠራተኞችን መረጃ የማረጋገጥ ሥራ ሊተገበር ነው።