
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት የመሶብ፣ የኮደርስ፣ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ እና ሌሎች ኢኒሸቲቦችን ማስፋት ላይ በትኩረት እየሠራች ነው።
የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የግለሰብ መረጃዎችን በዲጂታል መልክ በማከማቸት በቀላሉ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል ተግባር ነው።
🇪🇹የዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ ጥቅሞች
✅አገልግሎቶችን በፍጥነት ለማግኘት ያግዛል።
✅የደኅንነት ጥራትን ይጨምራል።
✅የፋይናንስ አገልግሎትን ለማሻሻል እና ብልሹ አሠራርን ለማስቀረት ያግዛል።
✅ የዲጂታል ግብይትን በማሳለጥ የኢኮኖሚ ዕድገትን ያፋጥናል።
✅ጊዜ እና ወጭን በመቀነስ በየትኛውም ቦታ አገልግሎትን ለማግኘት ያስችላል።
የአማራ ክልል የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አሥተባባሪ በላይ ዘለቀ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ዜጎች በሀገሪቱ በየትኛውም ቦታ ተንቀሳቅሰው እንዲሠሩ እና በሁሉም ቦታ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።
በክልሉ አርሶ አደሮችን ጨምሮ ማኅበረሰቡ የዲጂታል መታወቂያን እያወጣ እና ምዝገባ እያከናወነ መኾኑንም አንስተዋል።
ማኅበረሰቡ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን ለማውጣት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ውጤት እያሳየ መኾኑንም ገልጸዋል። ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።
በ2018 በጀት ዓመት 15 ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ እንዲያወጡ እየተሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል።
#አሚኮ #Digital_Ethiopia 2030
#MESOB_Ethiopia #Coders_ #NationalID #Ethiopia
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
