
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የከተሞችን ዕድገት የሚመጥን የኮሪደር ልማት እየተተገበረ መኾኑን የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ አማካሪ ሽቤ ክንዴ ተናግረዋል።
ማኅበረሰቡ የኮሪደር ልማትን በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በሀሳብ እና በቁሳቁስ እየደገፈ መኾኑንም ተናግረዋል። ይህ ማለት ግን ክፍተቶች አይኖሩም ማለት አይደለም፤ ችግሮችን እየለየን በየጊዜው እየፈታን ልማቱን አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት።
🔑የማኅበረሰብ ቅሬታን ከመፍታት አኳያ
👉 የኮሪደር ልማት አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ የመፍጠር እና የመግባባት ሥራ ቀድሞ ተሠርቷል።
👉 በኮሪደሩ ለሚነሱ ነዋሪዎች ከዘጠኝ ወራት ቀድሞ መረጃ የመሥጠት እና ዝግጅት እንዲያደርጉ የማሳወቅ ሥራ ተከናውኗል።
👉 በትላልቅ ከተሞች በተወሰነ መልኩ ይዞታቸው የሚነካባቸውን ነዋሪዎች ከሥራ ሳይስተጓጎሉ ጎን ለጎን በፍጥነት ኮሪደሩን የማጠናቀቅ ሥራ ተከናውሯል። በባሕርዳር፣ ጎንደር እና ሌሎች ከተሞች ይሄ ተሞክሮ ታይቷል።
👉 ከይዞታቸው ሙሉ በሙሉ ለሚነሱ ነዋሪዎች በሕጉ መሠረት ትክ ቦታ እየተሰጣቸው እና ካሣ እየተከፈላቸውም ነው።
👉 በቀበሌ ቤት ይኖሩ ለነበሩ ሰዎችም በከተማው መሥፈርት ትክ ቤት በመስጠት ነዋሪው ኮሪደሩ መጣብን ሳይኾን መጣልን በማለት በአወንታ እንዲቀበለው እየተሠራ ስለመኾኑ አንስተዋል።
🏙 አሁን ላይ ያለው የኮሪደር ልማት ማኅበረሰባዊ ቅቡልነት እና የተጠናከረ ድጋፍ ያለውም ነው።
👉ኮሪደር የከተሞችን ገጽታ መቀየሩን፣ ኢኮኖሚን ማነቃቃቱን፣ የኑሮ ዘይቤን ማሻሻሉን ኹሉም እየተረዳው መጥቷል።
👉 ትናንሽ ከተሞች በራሳቸው አቅም የኮሪደር ልማትን እየተገበሩ ነው።
👉 የከተሞች ማዘጋጃ ቤት
ጭምር ኮሪደር ልማትን ለመተግበር እየተንቀሳቀሱ እና ልምድ እየወሰዱ ነው።
👉 የጸጥታ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ሲቀረፍ ከተሞች በሰፊው ወደ ልማቱ የሚገቡበት ሁኔታ ይፈጠራል።
👉 በቀጣይ በሌሎች አካባቢዎች የሚታዩ ቴክኖሎጅዎችን ወደ ክልሉ በማስገባት ኮሪደሩን ለማስፋት እንደሚሠራ ተገልጿል።
ኮሪደር ልማት መነሻው የከተሞችን ገጽታ በመቀየር የዜጎችን አኗኗር እና አስተሳሰብ መለወጥ መዳረሻውን ደግሞ ኢትዮጵያን ወደተሟላ ብልጽግና ማሸጋገር ነው።
በአማራ ክልልም ይህ ዓላማ ተይዞ በክልሉ 32 ከተሞች እየተተገበረ እና በርካታ ውጤቶች እየተመዘገቡበት ይገኛሉ።
#ኮሪደር_ለትውልድ_የሚሻገር_ሥራ !
ዘጋቢ፦አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
