መሪዎች የብልጽግና ፓርቲ እሳቤዎችን በተግባር በመተርጎም ውጤታማ የመንግሥት እና የፓርቲ ተግባራትን አከናውነዋል።

3
የሐረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌቱ ወዬሳ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ የፓርቲ እና የመንግሥት ተግባራትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በበጀት ዓመቱ የፓርቲውን እሳቤዎች በተግባር በመተርጎም ረገድ አበረታች እና ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ኀላፊው ገልጸዋል።
አቶ ጌቱ ወዬሳ እንዳሉት ባለፈው በጀት ዓመት በርካታ አወንታዊ እና ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት።
ፓርቲውን በአሠራር፣ በሰው ኀይል እና በአደረጃጀት የማጠናከር ሥራ ስለመሠራቱም አስገንዝበዋል። አባላት እና መሪዎች በፓርቲው እሳቤዎች እና አቋሞች ላይ የጠራ ግንዛቤ እና የአስተሳሰብ አንድነት እንዲኖራቸው ስለመደረጉም ኀላፊው ጠቁመዋል።
ገዥ ትርክት እና ቅቡልነት እንዲረጋገጥ በትኩረት በመሠራቱ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ አዎንታዊ ስኬቶች ተመዝግበዋልም ብለዋል።
ፓርቲው ለአባላት የተግባር ተልዕኮ በመስጠት እና በተቋማዊ አቅም ርብርብ በማድረግ ለሐረሪ ክልል ፈጣን ዕድገት ጉልህ አሻራ ማሳረፍ ስለመቻሉም ነው ያስገነዘቡት።
በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ዕቅዶች እንዲሁም የ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ግቦች በስኬት መጠናቀቃቸውንም በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
በሁሉም የፓርቲ መዋቅሮች ውስጥ የሴቶች እና የወጣቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የማሳደግ ሥራም በስኬት ተከናውኗል ነው ያሉት።
በቀጣይም መሪዎች የተገኙ ስኬቶችን ይበልጥ በማጠናከር የብልጽግና ጉዞ ግቦች እንዲሳኩ በላቀ ቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም አቶ ጌቱ ጠቁመዋል።
በቀጣይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል ያሉትን ጉዳይ ሲያብራሩ እንዳሉት በመርህ ላይ የተመሠረቱ እና ሥራን ማዕከል ያደረጉ ትግሎችን ማጠናከር ይገባል።
የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የሕዝብን እርካታ ማሳደግ ሌላው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ስለመኾኑ አስገንዝበዋል።
ብልሹ አሠራሮችን እና ሙስናን በቁርጠኝነት ማስወገድም እንደሚገባ በመግለጫቸው በአጽንኦት ተናግረዋል።
በየዘርፉ የተመዘገቡ ድሎች በሙሉ በቁርጠኛ አመራር የተመሩ፣ የሁሉም አባላት እና ደጋፊዎች አሻራ ያረፈባቸው ውጤቶች ስለመኾናቸውም አስረድተዋል።
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleአምራች እና ሻጭን በቀጥታ የሚያገናኙ የገበያ ማዕከላት ግንባታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።
Next articleኢትዮጵያውያን ሁሉ ከልብ መነጋገርን ሽተው ያለልዩነት የተገናኙበት ታላቅ ቂድረክ!