ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ለሥራ ጉብኝት ኮምቦልቻ ገብተዋል።

12
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብዝኃ ሃይማኖትና ባሕል መገኛ፣ የፍቅርና የአብሮነት ተምሳሌት፣ የአራቱ ቅኝቶች መፍለቂያ፣ የታሪክ ማህደሯ ምድር ወሎ ገብተናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል።
እንደ ቦርከና ወንዝ የማይነጥፈው ገራገርነታችሁ፣ የማይጠገብ ትኅትናችሁ፣ እንደ ጦሳ ተራራ የገዘፈው መስተንግዶና ደማቅ አቀባበላችሁ ልባችንን በሐሴት ሞልቶታል ነው ያሉት።
ደሴ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለወሎ ሕዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበጎንጅ ቆለላ ወረዳ የመራጮች ምዝገባ በንቃት እየተካሄደ ነው።