
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን በጎንጅ ቆለላ ወረዳ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች እየተከናወነ ይገኛል።
ምዝገባው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ የወረዳው ነዋሪዎች የዜግነት ኀላፊነታቸውን ለመወጣት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመውጣት ካርድ በመውሰድ ላይ ናቸው። ሂደቱ በቴክኒክና በቁሳቁስ ዝግጅት የታገዘ በመሆኑ ምዝገባው ያለምንም መስተጓጎል እየተካሄደ መኾኑ ተመላክቷል።
እድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የኾኑ፣ እንዲሁም በወረዳው ውስጥ በቋሚነት የሚኖሩ ዜጎች ሕጋዊ መታወቂያቸውን በማቅረብ እየተመዘገቡ መኾኑን የኸረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ጠቁሟል።
ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሰረት ነው። ድምጽ መስጠት ደግሞ መብት ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚበረከት የዜግነት ኀላፊነት ጭምር ነው።
በምርጫዬ የሞባይል መተግበሪያ ራስዎን ለመራጭነት ይመዝግቡ!
● ከአፕ-ስቶር:- https://url-shortener.me/IHPC
● ከፕለይ-ስቶር https://url-shortener.me/IHPF ላይ በማውረድ ወይም
●በድረ-ገጽ አማራጭ (በቀጥታ) https://url-shortener.me/IHPH ይመዝገቡ።
የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ተግባራዊ የሚደረግባቸውን ምርጫ ጣቢያዎች በአስተያየት መስጫ ሣጥን ውስጥ ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ያገኛሉ። በቀሪ ምርጫ ጣቢያዎች የማንዋል የምዝገባ ሥርዓት ተግባራዊ ይሆናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
